በማዕዶት ለኢትዮጵያ ላይ ለመስራት

ጊዜው አሁን ነው

ጊዜው አሁን ነው

ማዕዶት ለኢትዮጵያ ኪነጥበብ ፕሮግራም

ኪነ- ጥበብ ለሰው ልጅ ሀሳብ ማንሸራሸርያ መሳርያ ሆኖ ማገልገል ከጀመረ ብዙ ጊዜያትን አስቆጥሯል፡፡ በተለይም ባደጉት ሀገራት ባህልን፣ታሪክን እምትን ፣ወግን እንዲሁም ልምድን ከማስጨበጥ አልፎ የሀገራት የኢኮኖሚ ምንጭ ከሆነ ሰነባብቷል፡፡ በሀገራችን እንደዉጭዎቹም ባይሆንም እጅግ ብዙ ስራ ተሰርቶበታል፡፡ የዚህ ሁሉ ባለቤት ማን ነች ብለን ካሰብ ሁላችንም ወዳደግንበት ቅድስት ቤተክርስቲያን መለስ እንላለን፡፡ በተለይም በኪነጥበቡ መስክ ያሉ ሰወችን መነሻቸውን ስንመለከት አብዛኞቹ ደራሲዎች፣ አዘጋጆች፣ሰዓሊዎች፣ተዋንያኖች፣ሙዚቀኞች የፊልም ባለሞያዎች መነሻቸው ቤተክርስቲያን እንደሆነ ሲናገሩ ይደመጣሉ፡፡ ለዚህም የያሬድ ዝማሬው፣ ድጓው፣ፆመ ድጓው፣ቅዳሴው፣ ማህሌቱ፣ዋዜማው፣መወድሱ፣ ቅኔው ሁሉም ለኪነጥበቡ ምቹ እንዶሆነ እሙን ነው፡፡ ታዲያ ቤተክርስቲያን ለነዚህ አይነቶቹ መርኃግብሮች ባለቤትነቷ ተነግሯል ወይ ቢባል ምንም እንዳለተባለ እናያለን፡፡ ለዚህም ሲባል ኢቲ አርት ሚዲያ በሀገራችን የመጀመርያ የሆነውን እጅግ ሰፊ መርኃግብር ያስጀመረ ሲሆን እጅግ ትልቅ መነቃቃትን ፈጥሯል፡፡

ድርጅቶ ይህን ፕሮግራም ቢደግፍ የሚያገኘው ጥቅም

በዚህ መርኃግብር ላይ ድርጅቶ ስፖንሰር ቢያደርግ የሚያኘው ጥቅም ፕሮግራሙ እጅግ ሰፊ ከመሆኑ ባሻገር ከ2500 በላይ ሰው የሚገኝበትም ጭምር ስለሆነ እንዲሁም ብዙ ተመልካች ባላው በኢቲ አርት ሚዲያ የሚተላለፍ መርኃግብር ስለሆነ ድርጅቶ አልያም የሚሰሩት ስራ ከሚመጣው ሰው ባሻር በሚዲያው የሚመለከተው ሰው ብዙ በመሆኑ ጥቅሙ እጅግ ሰፊ ነው፡፡ በተጨማሪም እጅግ ብዙ የክብር እንግዶች የሚገኙ ሲሆን የምስጋና እና የሰርተፊኬት ፕሮግራምም ለድርጅቶ በብፁዐን ሊቃነ ጳጳሳት ፊት የሚቀርብ ይሆናል፡፡ በዚህ ፕርግራም ላይ አሻራዎን ቢጥሉ ወጣቱን ከማስተማር እንፃር እና በእምነቱ እንዲፃና ከሚያገኘው መንፈሳዊ ጥቅም አኳያ ለቅድስት ቤተክርስትያን እና ለምዕመና ትልቅ የበረከት ስራም እንደሚሰሩ ለማሳወቅ እንወዳለን:: በተጨማሪም የትኬት ገቢዉ ለሻሸመኔ ተጎጂዎች ስለሚሆን አሻራዎን ይጥላሉ፡፡

ማዕዶት ለኢትዮጵያ

ማዕዶት ማለት መሻገር ማለት ሲሆን አንድ ላይ ማዕዶት ለኢትዮጵያ ሲባል ለኢቲዮጵያ መሻገር ማለት የሚለውን ትርጉም ይሰጣል፡፡ ስለዚህም በእለቱም ኦርቶዶክሳዊ ወጣት በ2016 ወደ ቅድስት ቤተክርስቲያን ይመለስ የሚል ትልቅ ሀሳብ አለው፡፡

የፕሮግራሙ ዓለማ

የፕሮግራሙ ዓለማ ማዕዶት ለኢትዮጵያ የተሰኘው ይህ መንፈሳዊ የኪነ ጥበብ መርኃግብር ዋና አላማው መጪዉን ዘመን በተስፋ እንድንሻግር የሚያደርጉ መርኃግብሮችን ማስተላለፍ ሲሆን በተጨማሪም - ቅድስት ቤተክርስቲያ ከዓዉደምህረት መርኃግብሮች ባለፈ በንደዚህ አይነት መርኃግሮችም እንዳለች የማሳየት - ተስፋን የማሰነቅ - አዲሱን ዓመት ክፋትን ትተን ሀሴት እና ደስታን የሞላበት ትምህርት የማስተማር - የኪነጥበብ መነሻዋ ቤተክርስቲያን እንደሆነችም የማሳየት ዓላማ አለው - ኦርቶዶክሳዊ ወጣት በትምህርት ታንፀው ወደ በታቸው እንዲመለሱ

ማዕዶት ለኢትዮጵያ

CONTACT US

በማዕዶት ለኢትዮጵያ ላይ ለመስራት ጊዜው አሁን ነው ኪነጥበብ ፕሮግራምን በተለያዩ መንገድ ለመደገፍ እና አብሮ ለመስራት የምትፈልጉ ያናግሩን